Fana: At a Speed of Life!

በሀገራዊ የምክክር መድረኩ የሚደረስበትን ስምምነት ለማክበር ቁርጠኝነት ያስፈልጋል – የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 27፣ 2014 ( ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የሚደረገው ሀገራዊ ምክክር ስኬታማ እንዲሆን መንግስት፣ ልሂቃን፣የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሁሉም ተሳታፊዎች የመጨረሻውን ስምምነት የማክበር ሃላፊነት አለባቸው ሲሉ የፖለቲካል ሳይንስ ምሁራን ገለጹ፡፡

በኮተቤ ትምህርት ዩንቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር አየነው ብርሀኑ÷ በሚደረገው ሀገራዊ ምክክር ሁሉም ተሳታፊዎች በሀሳብ የበላይነት ለማመን እንዲሁም የሚደረስበትን ውጤት ለመቀበል ቁርጠኛ መሆን ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በውይይቱ የሚሳተፉ አካላት በሚነሱ ጉዳዮች ላይ በሰከነ መንፈስ ጥልቅ ውይይት በማድረግ ሀገሪቱን ካለችበት ችግር ለማሻገር ሃላፊነታቸውን መወጣት ይኖባቸዋል ያሉት ደግሞ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶክተር ንጉስ በላይ ናቸው፡፡

በኢትዮጵያ የሚታዩ የሀሳብ ልዩነቶችን በውይይት ለማቀራረብ እስካሁን አለመሰራቱ ልዩነቶቹ እንዲሰፉ ከማድረጉም ባላይ አሁን ሀገሪቱ ላለችበት ችግር እንድትጋለጥ ምክንያት መሆኑን ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይ የሚደረገው ብሔራዊ ምክክርም ኢትዮጵያ አሁን ካለችበት ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ሊያጋጥማት ከሚችለው ችግር እንድትወጣ የሚያግዝ መሆኑንም ነው ምሁራኑ የጠቆሙት፡፡

በተስፋየ ምሬሳ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.