Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሩን ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቀለች

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ዋንጫ ካሜሩን ጋምቢያን በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን ተቀላቅላለች፡፡
 
ምሽቱን በተካሄደው ጨዋታ ካሜሩን ጋምቢያን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ ግማሽ ፍጻሜውን የተቀላቀለች የመጀመሪያዋ አገር ሆናለች፡፡
 
የካሜሩን የማሸነፊ ግቦች የፊት መስመር አጥቂው ቶኮ ኢካምቢ በ50 እና 57ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡
 
የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ ምሽት 4 ሰዓት ላይ ቡርኪናፋሶ እና ቱኒዚያ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል፡፡
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.