Fana: At a Speed of Life!

በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አለፈች

አዲስ አበባ፣ ጥር 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሴቶች ከ20 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ኢትዮጵያ ታንዛኒያን 2 ለ 0 በማሸነፍ ወደ ቀጣዩ ዙር አልፋለች፡፡
 
የኢትዮጵያ ከ 20 ዓመት በታች ሴቶች ብሄራዊ ቡድን በታንዛኒያ አቻው 1 ለ 0 ቢሸነፍም ዛሬ በተደረገው ጨዋታ 2 ለ0 በማሸነፍ 2 ለ 1 በሆነ ድምር ዉጤት ወደ መጨረሻው ዙር ማለፍ ችሏል፡፡
 
በአበበ ቢቄላ ስታዲዮም በተካሄደው ጨዋታ የኢትዮጵያን የማሸነፊያ ግቦች ረዴት አስረሳኸኝ አስቆጥራለች።
 
በሚኪያስ አየለ
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.