ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትንሳኤ በዓልን አስመልክተው ባስተላለፉት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት÷ ትንሳኤ ሞትንና መቃብርን የማሸነፍ በዓል መሆኑን ገልጸዋል፡፡
የክርስቶስ መነሳት ተዘግቶ የሚቀር ነገር እንደሌለ ከሞት ወዲያ ሕይወት፣ ከመቃብር ወዲያ ትንሳኤ መኖሩን አስተምሮናል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ኢትዮጵያም አለቀች፣ ደቀቀች፣ ተጠናቀቀች፣ ሞተች፣ ተቀበረች ያሏትን ሁሉ አሳፍራ እየተነሳች ነው፤ መግነዟን ፈትታ፣ ሞቷን ድል ነስታ፣ መቃብሯን ትታ በሁሉም ነገሯ እየተነሣች ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
ከትንሳኤ በኋላ ዳግም ሞት እንደሌለ፤ ኢትዮጵያም ከዚህ በኋላ ከፍ ከፍ ትላለች እንጂ ሞት ዳግም አያገኛትም ሲሉም አስረድተዋል፡፡