Fana: At a Speed of Life!

የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር መሠረት ያደረጉ የሰብል ዓይነቶችን በስፋት ማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና ይጫወታል – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር መሠረት ያደረጉ የሰብል ዓይነቶችን በስፋትና በጥራት እንዲመረቱ ማስቻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን ለመተካት እና ገቢን ለማሣደግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጅማ ዞን ጌራ ወረዳ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ማሳ የጎበኙ ሲሆን፥ ይህን ተከትሎ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በጅማ ዞን እና ከተማ ዙሪያ በመልማት ላይ የሚገኙ የቡና እና የበጋ የመስኖ ስንዴ ኩታ ገጠም እርሻዎች ምርት አበረታች ውጤት ማስገኘቱን አስታውቀዋል፡፡

የአካባቢን ሥነ-ምኅዳር መሠረት ያደረጉ የሰብል ዓይነቶችን በስፋትና በጥራት እንዲመረቱ ማስቻል የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ፣ ከውጭ የሚገባ ምርትን ለመተካት እና ገቢን ለማሣደግ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወትም ነው ያመለከቱት፡፡

 

በመስክ ጉብኝቱ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋርም በቀጠናው የዓለም ባንክ ዳይሬክተርና በተመድ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።

በአልአዛር ታደለ እና ሙክታር ጠሃ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.