Fana: At a Speed of Life!

የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በሶማሊያ ግዳጅ አፈጻጸም ዙሪያ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ኢትዮጵያ የመጡት ″በአሚሶም‶ ግዳጅ ተሳታፊ የሆኑ የምስራቅ አፍሪካ አገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ ሰብሳቢነት መክረዋል።
 
ምክክሩ ከሶማሊያ ግዳጅ ጋር በተያያዘ የጋራ አረዳድ ለመያዝ ያለመ መሆኑ ነው የተገለጸው።
 
በውይይታቸውም በሶማሊያ ስላለው ሃይል እንቅስቃሴና ለቀጣይ መደረግ ስላለበት ጉዳይ በጥልቀት መምከራቸው ተመላክቷል፡፡
 
አሁን ላይም በአፍሪካ ህብረት የባለድርሻ አካላት ውይይት እየተካሄደ መሆኑም ተመላክቷል፡፡
 
በውይይቱ የኢትዮጵያን ጨምሮ የኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ቡሩንዲ እና ሶማሊያ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች አና የጅቡቲ ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር የአሚሶም ፎርስ ኮማንደር መሳተፋቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.