Fana: At a Speed of Life!

በቦረና ተጨማሪ ድጋፍ እንዲቀርብላቸው የድርቅ ተጎጂዎች ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ቦረና ዞን የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ የተለያዩ አካላት ድጋፍ ቢያደርጉም በቂ ባለመሆኑ ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የዞኑ ነዋሪዎች ጠየቁ፡፡
 
ድርቁ በዞኑ 13 ወረዳዎችና 2 ከተማ አስተዳደሮች የተከሰተ ሲሆን÷ ድርቁን ተከትሎ የሞቱና በሞት አፋፍ የሚገኙ እንስሳት ቁጥር 7 መቶ ሺህ እንደደረሰ ነው የተገለጸው።
 
የዝናብ እጥረትን ተከትሎ ችግሩ የተከሰተ ሲሆን÷ የቦረና እንስሳት ሀብት 6 ነጥብ 8 ሚሊየን ይደርስ ነበርም ተብሏል።
 
የዞኑ የውሃ ሽፋን ከነበረበት 53 በመቶ ወደ 28 ነጥብ 6 በመቶ መቀነሱም ተመላክቷል።
 
የዞኑ ነዋሪዎች ድርቁ ከፍተኛ ጫናና ማህበራዊ ቀውስ እንዳሳደረባቸውም ተናግረዋል።
 
እንስሳቱን ለመሸጥ ቢፈልጉ እንኳን በቂ ዋጋ እንደማያስገኙላቸው የገለጹ ሲሆን፥ የእርዳታ ፈላጊ ዜጎች ቁጥር ጨምሯል።
 
ሆኖም በተለያዩ አካላት ድጋፍ ቢደረግም በቂ ባለመሆኑ ነው ተጨማሪ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የጠየቁት።
 
በአፈወርቅ እያዩና ታሪኩ ለገሰ
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.