Fana: At a Speed of Life!

በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፤የካቲት 8፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ13ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ ሀዋሳ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ድል ቀንቷቸዋል።
ቀን 10 ሰዓት ላይ በተካሄደው የፋሲል ከነማ እና ሀዋሳ ከተማ ጨዋታ በሀዋሳ ከተማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
የፋሲል ከነማው ተከላካይ ከድር ኩሊባሊ በራሱ መረብ ላይ ባስቆጠረው ጎል ሀዋሳ ሲመራ ቢቆይም ከረፍት መልስ ፍፁም አለሙ ባስቆጠራት ጎል ፋሲል አቻ መሆን ችሎ ነበር፡፡
ይሁን እንጅ የፋሲል ከነማ ተከላካዮችን ክፍተት ተጠቅሞ ወንድማገኝ ሀይሉ በ86ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ጎል ሀዋሳ ከተማ ከጨዋታው ሙሉ 3 ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል፡፡
ከጨዋታው መጠናቀቅ በሁዋላ የአፄዎቹ አስልጣኝ ስዩም ከበደ ለሽንፈታቸው የአጥቂ ክፍላቸውን ወቅሰዋል፡፡
የሀዋሳ ከተማው አሰልጣኝ ዘራዕይ ሙሉ በበኩላቸው፥ የአምናውን ሻምፒዮን በማሸነፋቸው መደሰታቸውን ገልፀዋል።
በተለይም የፋሲልን ድክመት ለይተን ማወቃችን ጨዋታውን እንድናሸንፍ ረድቶናል ነው ያሉት።
ምሽት አንድ ሰዓት ላይ በተካሄደው የሰበታ ከነማ እና የአዲስ አበባ ከተማ ጨዋታ በአዲስ አበባ ከተማ 5 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.