Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ጣሊያን በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጣሊያን በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እና ፋሽን ኢንዱስትሪ በጋራ ለመስራት ተስማሙ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር አጎስቲዮኖ ፓሌሴ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ እና ጣሊያን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ትስስር እንዳላቸው ገልጸው ፥ ይህ ትስስር የበለጠ ሊሻሻል እንደሚገባ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የዘርፉን ምርታማነት፣ ጥራትና ተወዳዳሪነት በማሳደግ የለውጡን ምዕራፍ በማፋጠን የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መናኸሪያ የመሆን እጅግ የላቀ እቅድ እንዳለውም ነው የተናገሩት።

ይህንን እቅድ ለማሳካትም አራት የተቀናጁ የአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መገንባታቸውን ገልጸዋል። ከእነዚህ ውስጥ ሶስቱ ተመርቀው ስራ የጀመሩ ሲሆን ፥ እነዚህን ፓርኮች የመምራት ኃላፊነት የተሰጠው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፓርኮቹን የመደገፍ፣ የመገምገም እና የእድገት ደረጃ ሪፖርት የማድረግ ስራ እየሰራ መሆኑንም ሚኒስትሩ አስታውቃዋል።

ለቀጣይም የኢትዮጵያ መንግስት ቀስ በቀስ ገበያ የመክፈት ፍልስፍናን በመከተል ንቁ ኢኮኖሚ ለመፍጠር ማቀዱንም ነው አቶ መላኩ የተናገሩት።

በኢትዮጵያ የጣሊያን አምባሳደር በበኩላቸው፥ ሁለቱ ሀገራት ጥልቅ ኢኮኖሚያዊ ትስስር እንዳላቸው የተናገሩ ሲሆን ፥ የሃገራቱ ጥልቅ የኢኮኖሚ ውህደትም ወደ ተግባራዊ የኢኮኖሚ ግንኙነት መቀየር እንዳለበት አመላክተዋል።

ኢትዮጵያ 115 ሚሊየን ህዝብ ያለባት ሀገር እንደመሆኗ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥን እውን ለማድረግ እና የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው ለመስፋፋት ወርቃማ እድል መሆኑንም ነው ያነሱት።

አምባሳደሩ አክለውም ፥ ሀገራቸው ጣሊያን በአግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲሁም በፋሽን ኢንዱስትሪ ጥሩ ልምድ ያላት መሆኗን አንስተው ፥ የጣሊያን መንግስትም የቴክኒክ ድጋፍ እና ልምድ ለመካፈል ዝግጁ መሆኑን መግለጻቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.