Fana: At a Speed of Life!

የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዲያ ሆሳና ይጫወታል

አዲስ አበባ፣የካቲት 10፣2014 (ኤፍ ቢሲ) 13ኛ ሳምንት የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርምየር ሊግ ጨዋታዎች ሲቀጥሉ መሪው ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሀዲያ ሆሳና የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡
እስካሁን በተደረጉ ጨዋታዎች ሽንፈት ያልገጠመው ቅዱስ ጊዮርጊስ ደረጃውን ለማስጠበቅ እና ከተከታዮቹ ሀዋሳ ከተማ እና ፋሲል ከተማ ያለውን ነጥብ ለማስፋት ወደ ሜዳ የሚገባ ይሆናል፡፡
ከወልቂጤ ከተማ ጋር በእኩል 16 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሀዲያ ሆሳዕና ደግሞ ደረጃውን ለማሻሻል ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል፡፡
በሊጉ በተደረጉ ጨዋታዎች 20 ጎል ያስቆጠረዉ የቅዱስ ጊዮርጊስ ያጥቂ ክፍል ሀዲያ ሆሳዕናን በቀላሉ ያሽንፋል ተብሎ ግምት የተሰጠዉ ቢሆንም ነብሮቹ ካደረጉት 4 ጨዋታዎች በመነሳት ለጊዮርጊስ ቀላል ተጋጣሚ እንደማይሆኑ ይጠበቃል፡፡
ፈረሰኞቹ ከረጅም ጊዜ ጉዳት በኋላ አዲስ ግደይን የሚያገኙ ሲሆን፥ በአንፃሩ ከንዓን ማርክነህ ከጉዳቱ ባለማገገሙ በዛሬዉ ጨዋታ እንደማይሰለፍ ተረጋግጧል፡፡
ሀዲያ ሆሳና በአንጻሩ አስቻለው ግርማን ከግል ጉዳይ እና ኤፍሬም ዘካሪያስን ከጉዳት መልስ በዛሬዉ ጨዋታ የሚያገኝ ሲሆን በግል ጉዳይ ከቡድኑ ጋር ያልነበረዉ መላኩ ወልዴ በዛሬዉ ጨዋታ አይሰለፍም፡፡
ሊጉ ቀጥሎ ሲካሄድ ምሽት 1 ሰዓት ላይ አዳማ ከተማ ከመከላከያ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.