Fana: At a Speed of Life!

በፓን አፍሪካ ትምህርት ቤቶች ውድድር ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓን አፍሪካ ትምህርት ቤቶች ውድድርን ኢትዮጵያ በሁለቱም ፆታ ያደረገቻቸውን ጨዋታዎች አሸንፋለች፡፡

በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ አስተናጋጅነት ዛሬ የተጀመረው የፓን አፍሪካ የትምህርት ቤቶች ውድድር በተለያዩ ጨዋታዎች በሁለቱም ፆታዎች ተሳታፊ የሆነችው ኢትዮጵያ ድል ማስመዝገቧ ተገልጿል።

በወንዶች አስተናጋጇ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን የገጠመችው ኢትዮጵያ 2 ለ 1 ስታሸንፍ በሴቶች ደግሞ ሴኔጋልን 2 ለ 0 በማሸነፍ ውድድሩን ጀምራለች ነው የተባለው።

ውድድሩ ከሰዓት በኋላ ሲቀጥል ኢትዮጵያ በወንዶች ከቤኒን 11፡00 ፣ በሴቶችም በተመሳሳይ ከቤኒን 12፡30 ላይ እንደምትጫወት ከእግር ኳስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.