Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሪያ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ 380 የውጭ ሃገር ዜጎችን ወደ ማቆያ ስፍራ አስገባች

አዲስ አበባ፣ የካቲት 16፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰሜን ኮሪያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን በመስጋት 380 የተለያዩ ሃገራት ዜጎችን ወደ ማቆያ ስፍራ ማስገባቷ ተነገረ።

ወደ ማቆያ ስፍራ የተወሰዱት አብዛኛዎቹ የውጭ ሃገር ዜጎች ዲፕሎማቶች ሲሆኑ በዋና ከተማዋ ፒዮንግያንግ በሚገኝ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆዩ ይደረጋል ተብሏል።

200 አካባቢ የሚሆኑ የውጭ ዜጎች በቫይረሱ ምክንያት ለአንድ ወር ያክል ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገው እንደነበር ይታወሳል።

ከቤት የመውጣት ክልከላው ከተጠናቀቀ በኋላም ወደ ማቆያ ስፍራዎች እንዲገቡ ተደርጓል ነው የተባለው።

ሰዎቹ ለምን ያክል ጊዜ በማቆያ ጣቢያው እንደሚቆዩ ግን የተባለ ነገር የለም።

በሰሜን ኮሪያ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው መኖሩን የሚያመላክት መረጃ እስካሁን አልተገኘም።

ይሁን እንጅ በጎረቤት ደቡብ ኮሪያ ሰባት ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸውን ሲያጡ 763 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

ከዚህ ባለፈም 11 የሃገሪቱ ጦር አባላት በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ፥ 7 ሺህ 700 ወታደሮች በለይቶ ማቆያ ስፍራ ውስጥ ይገኛሉ ነው የተባለው።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.