Fana: At a Speed of Life!

በሸዶች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ልዩ ስሙ መብራት ኃይል አካባቢ በሚገኝ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ በሰባት የመስሪያ ሼዶች ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ።
በኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ እንደገለጹት÷ በአደጋዉ 4 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት የወደመ ሲሆን÷ 20 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ንብረት ማዳን ተችሏል፡፡
አደጋውን ለመቆጣጠር 8 የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪዎች እና 55 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ስምሪት መሰጠቱን ጠቁመው÷ እሳቱን ለማጥፋትም 141 ሺህ ሊትር ውኃ እና 5 ሺህ ሊትር ኬሚካል ፎም ጥቅም ላይ ውሏል ብለዋል፡፡
ትላንት ሌሊት 7:15 ባጋጠመው የእሳት አደጋ ሁለት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱንም ነው አቶ ንጋቱ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የገለጹት፡፡
አደጋውን ሙሉ ለሙሉ ለመቆጣጠር አምስት ሰዓት መፍጀቱንም ነው ጨምረው የገለጹት፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.