Fana: At a Speed of Life!

4ኛው የአፍሪካ ወጣቶች ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 4ኛውን የአፍሪካ ወጣቶች ዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በአዲስ አበባ ተጀመረ።
የፕላን እና ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ጥሩማር አባተ ጉባኤው ወጣቶች በአጀንዳ 2030 እና አጀንዳ 2063 ላይ ሊኖራቸው የሚችለው ሚና ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ብለዋል።
ወጣቶች ያላቸውን አቅም ተጠቅመው አዳዲስ የመፍትሄ አማራጮችን ለማበልጸግ ቁልፍ ሚና መጫወት እንደሚችሉ ጠቁመው÷ ይህም ፈተናዎችን ለማሸነፍ የሚያግዝ መሆኑ አመላክተዋል፡፡
ወጣቶች ይህን ሚና እንዲወጡ አቅማቸውን ማሳደግ እንደሚያስፈልግ ገልጸው÷ ለዚህ ደግሞ ተገቢውን የፖሊሲ ማዕቀፍ በመንደፍ መድረኩን ማመቻቸት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ጉባኤው ዘላቂ የልማት ግቦች ላይ የሚያተኩር መሆኑ የተገለጸ ሲሆን÷ ወጣቶች በአጀንዳ 2030 እና አጀንዳ 2063 ላይ ሊኖራቸው የሚችለው ሚና በግልጽ መለየት ላይ ትኩረት ያደረገ ነውም ተብሏል፡፡
ዓለም አቀፍ እንዲሁም አህጉራዊ ግቦችን ለማሳካት ፖሊሲዎች እና ስትራቴጂዎች በበቂ መጠን አካታች መሆናቸው ላይ ግልጽ ውይይት እንደሚጠይቅም ሚኒስትር ዲኤታዋ ገልጸዋል፡፡
ኢትዮጵያን እንደ ምሣሌ በማንሳት በ10 ዓመት የልማት እቅድ ላይ ዘላቂ የልማት ግቦች እና አጀንዳ 2063ን ማካተቷን ተናግረዋል፡፡
የአፍሪካ የወጣቶች የዘላቂ የልማት ግቦች ጉባኤ በአህጉሩ የሚገኙ ወጣቶች ስለ ዘላቂ የልማት ግቦች የሚተዋወቁበትና በቀጣይ አተገባበሩ ላይ ተሳትፏቸውን ለማጎልበት የሚሠራ መሆኑን ከፕላንና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.