Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በኢትዮጵያ በግጭት ለተጎዱ ዜጎች የምግብና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 1 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች በቀይ ጨረቃ ማኅበር በኩል በኢትዮጵያ በተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች የሚውል 50 ቶን የምግብ አቅርቦት ድጋፍ እንዲሁም የሕጻናት አልሚ ምግቦችን ጨምሮ የሕክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ በኢትዮጵያ በተከሰተው ሰብዓዊ ቀውስ ከተለያየዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ በሺዎች ለሚቆጠሩ ወገኖች በተለይም ሴቶችና ሕጻናትን ለመታደግ ያለመ መሆኑን የኢሚሬቶች ቀይ ጨረቃ ማህበር አስታውቋል።

የኢሚሬቶች ቀይ ጨረቃ ማኅበር ዋና ፀሃፊ ዶክተር ሞሐመድ አቲቅ አል ፋላሂ፥ ኢትዮጵያ ባጋጠማት ሰብዓዊ ቀውስ ሁሉ የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ከጎኗ እንደቆመች እና ተጋላጭ ወገኖችን በመደገፍ ረገድም የበኩሏን ስትወጣ መቆየቷን ገልጸዋል፡፡

የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ቀይ ጨረቃ ማኅበር፥ በኢትዮጵያ መርሃ-ግብር ቀርጾ ኢትዮጵያውያንን ከ ተፈጥሮ አደጋ ለመታደግ የሰብዓዊነት ሥራዎች ሲያከናውን እንደቆየና የልማት ፕሮጀክቶችና እና የሰብዓዊ ድጋፍ መርሃ-ግብሮች ቀርጾ ሲሳተፍ መቆየቱንም ነው ሃላፊው ያስታወቁት፡፡

ማኅበሩ በቀጣይ በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሰብዓዊ ቀውስ እንዳይደርስ ለመታደግ እንደሚሠራ አስታውቋል፡፡

በተከሰተው ሰብአዊ ቀውስ የተፈናቀሉ ወገኖችን በአውሮፕላን ጭምር ለመድረስ እና መሠረታዊ አቅርቦቶችን ለማከፋፈል ማኅበሩ እንደሚሰራ ከተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.