Fana: At a Speed of Life!

በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሚሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን ሽኝት ተደረገ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለ18ኛ ጊዜ በሚካሄደው የሰርቢያ-ቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና
ለሚሳተፉ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት ዛሬ ምሽት አሸኛኘት ተደርጎላቸዋል።
 
በሽኝት መርሃ ግብሩ ላይ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መሥፍን ቸርነት እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ተገኝተዋል።
 
አምባሳደር መሥፍን ቸርነት እና ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ÷ለልዑካን ቡድኑ አባላት የሥራ መመሪያና የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል።
 
የአሰልጠኞችና የአትሌቶች ተወካዮችም ስለዝግጅታቸው አስተያየት የሰጡ ሲሆን÷ የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ መደረጉንም ከአትሌቲከክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.