Fana: At a Speed of Life!

ቻይና ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር ያላትን መደበኛ የንግድ ልውውጥ እንደምታስቀጥል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር ያላትን መደበኛ የንግድ ልውውጥ እና የኢኮኖሚ ትብብር እንደምታስቀጥል ገልጻለች፡፡
 
የቻይና ንግድ ሚኒስቴር እንዳስታወቀው÷ቻይና ከሩሲያ እና ዩክሬን ጋር ያላትን በእኩልነት፣ በጋራ ጥቅም እና መከባበር ላይ የተመሰረተ የንግድ እና የኢኮኖሚ ትብብር ትቀጥላለች ፡፡
 
በፈረንጆቹ 2022 የመጀመሪያዎቹ ሁለት ወራት የቻይና-ሩሲያ የንግድ ልውውጥ 26 ነጥብ 43 ቢሊየን ዶላር የደረሰ ሲሆን÷ የ38 ነጥብ 5 በመቶ አድገት ማሳየቱም ተገልጿል፡፡
 

ይህም ቻይና ለ12 ተከታታይ ዓመታት የሩሲያ ትልቋ የንግድ አጋር እንድትሆን አስችሏታል ነው የተባለው፡፡

በተመሳሳይ በ 2021 ቻይና ከዩክሬን የምታስገባቸው የገቢ ምርቶች ከ34 ቢለየን ዶላር ወደ 72 ነጥብ 82 ቢሊየን ዶላር ሲያሳድግ ወደ ዩክሬን የምትልከው ምርት ደግሞ ከ38 ነጥብ 4 ቢሊየን ወደ 68 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ማደጉ ተመላክቷል፡፡
ቻይና ባለፈው ዓመት ከዩክሬን ምርቶችን ከሚያስገቡ ሀገራት ቀዳሚ ስትሆን÷ 8 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን በአንድ ዓመት ውስጥ ማስገባት ችላለች፡፡
 
የዩክሬንን መንግስት ስታስቲክስ አገልግሎት መረጃን ጠቅሶ ሲ ጅ ቲ ኤን እንደዘገበው÷ ቻይና 10 ነጥብ 97 ቢሊየን ዶላር የሚያወጡ የቻይና ዕቃዎችን ለዩክሬን በማቅረብ ቀዳሚ ሀገር መሆን ችላለች፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.