Fana: At a Speed of Life!

የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ ከአለም አንደኛ በመሆን አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣መጋቢት 12፣2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ በ9 ሜዳሊያ ከአለም አንደኛ በመሆን ውድድሩን አጠናቃለች፡፡

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የሩጫ ዓይነቶች በሁለቱም ፆታ 4 ወርቅ፣ 3 ብር እና 2 ነሃስ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎችን ለሀገራቸው ማምጣት ችለዋል፡፡

ይህ ውጤትም የኢትዮጵያ ከፍተኛው የአለም የቤት ውስጥ ውድድር ውጤት ሆኖ መመዝገቡን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና አሜሪካ እና ስዊዘርላንድ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ በ2008 በተደረገው 12ኛው የቫሌንሽያ የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና 4 ወርቅ፣ 1 ብር፣ 1 ነሃስ ስታመጣ በ2018 በተካሄደው 17ኛው የበርሚንግሃም የአለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ደግሞ 4 ወርቅ፣ እና 1 የብር ሜዳሊያ ማምጣት መቻሏን ከፌደሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.