Fana: At a Speed of Life!

51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በመከላከያ ስፖርት ክለብ አሸናፊነት ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስድስት ተከታታይ ቀናት በሀዋሳ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 51ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በመከላከያ ስፖርት ክለብ አጠቃላይ አሸናፊነት ተጠናቀቀ።
ከመጋቢት 19 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ የተካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ፍፃሜውን ዛሬ አግኝቷል።
በዚህ ዉድድር መከላከያ አትሌቲክስ ክለብ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን ውድድሩን አጠናቋል።
እንዲሁም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሁለተኛ ደረጃ ይዞ ሲያጠናቅቅ ኦሮሚያ ክልል አትሌቲክስ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ጨርሷል።
በሻምፒዮናው መዝጊያ በአትሌቲክስ ስፖርት ቤተሰቡ ዘንድ ተጠባቂ የሆኑ 10 የፍፃሜ ውድድሮች ተካሂደዋል።
በዚህም 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ወንዶች ፍፃሜ ውድድር አትሌት አሊ አብዱለመና ከደቡብ ፖሊስ ቀዳሚ ሆኖ አጠናቋል።
ጥላሁን ኃይሌ ከደቡብ ፖሊስ ሁለተኛ ሲሆን ጌትነት ዋለ ከሲዳማ ቡና ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሩጫ ውድድር ፍፃሜ አትሌት ፈንታዬ በላይነህ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አንደኛ፤ ብርቱኳን ወልዴ ከሲዳማ ቡና ሁለተኛ፤ አትሌት መልክናት ውዱ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር ደግሞ አያል ዳኛቸው ከመከላከያ አንደኛ፣ ዳዊት ስዩም ከመከላከያ ሁለተኛ፤ ውብርስት አስቻለው አማራ ክልል አትሌቲክስ ቡድን ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል።
በወንዶች 1 ሺህ 500 ሜትር አትሌት አድሃና ካህሳይ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ መልካሙ ዘገየ ከሲዳማ ቡና፤ በድሩ ሱሩር ከደቡብ ፖሊስ እንደየቅደም ተከተላቸው ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ደረጃ ይዘው አጠናቀዋል።
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.