Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ድል ቀንቷቸዋል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 25፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በተካሄዱ የተለያዩ የማራቶን ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል።

በ2022 ኮሪያ -ዴጉ ዓለም አቀፍ ማራቶን ኢትዮጵያዊው አትሌት ሽፈራው ታምሩ አሸንፏል።

በፈረንሳይ፣ ፓሪስ ዓለም አቀፍ ማራቶን በወንዶቹ አትሌት ጫሉ ዴሶ ገልሜሳ 2 ሰዓት ከ5 ደቂቃ ከ7 ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት አሸናፊ ሲሆን ፥ ሌላኛው አትሌት ሰይፉ ቱራ 2ኛ ሆኖ በማጠናቀቅ የብር ሜዳሊያ አስገኝቷል።

በሴቶች አትሌት ፋንቱ ጂማ ሁለተኛ በመውጣት የብር ሜዳሊያ ስታገኝ አትሌት በሱ ሳዶ ደግሞ ውድድሩን በሶስተኝነት አጠናቃለች።

በባርሴሎና በተደረገ የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር አትሌት ሐፍቱ ተክሉ እና አትሌት ጫላ ረጋሳ በቅደም ተከተል አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

በተመሳሳይ በሴቶች ግማሽ ማራቶን አትሌት ጌጤ ዓለማየሁ ሁለተኛ፣ አትሌት አስናቀች አወቀ ሶስተኛ እና አትሌት ረድኤት ዳንኤል አራተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.