Fana: At a Speed of Life!

በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ያለውን የስራ ፈላጊዎች መሰረታዊ ጥያቄ ለመፍታት የሚያግዝ ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 26፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በከተሞች በከፍተኛ መጠን እየጨመረ ያለውን የስራ ፈላጊዎች መሰረታዊ ጥያቄ በጋራ ለመፍታት ያግዛል የተባለ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈረመ።

የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር ያደረጉት የመግባቢያ ስምምነት ብቃት ያለው የሰው ሃይል ለመግንባት በአጋርነት መስራት በማስፈለጉ መሆኑ በስነስርዓቱ ላይ ተጠቁሟል።

ከተሞች ያላቸውን ውስብስብ ባህሪ ታሳቢ በማድረግ የቀልጣፋ ምርትና አገልግሎት መፍለቂያ እንዲሆኑ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እንዲሻሻል፣ በከፍተኛ መጠን የስራ እድሎችንም ለመፍጠር የሚያግዝ የጋራ ስራ ይጠበቃል ተብሏል።

በስራ ቦታ የሙያ ደህንነትና ጤንነትን የሚያረጋግጡ አገልግሎቶችን ለማስፋፋትም አብሮ መስራቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል ።

\በተመሳሳይ የማዕድን ሚኒስቴር ከስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ጋር በሰው ሀይል ልማት፣ቴክኖሎጂ፣ስራ ፈጠራና የስራ አካባቢ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን አስመልክቶ የማዕድን ሚኒስትሩ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው የማዕድን የስራ ዘርፍ ዜጎችን በተገቢው መንገድ የሚጠቅምና የደህንነት ዋስትና የሚሰጥ ዘርፍ እንዲሆን በጋራ እንሰራለን ብለዋል።
ማዕድን በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የስራና የገቢ አማራጭ የሆነ ዘርፍ መሆኑንያነሱት ሚኒስትሩ ይህ ወሳኝ የስራ ዘርፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በተቀናጀ መልኩ ሲመራ ደግሞ ጥቅሙ ለዜጎችም ለሀገርም መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በበርናባስ ተስፋዬ

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.