Fana: At a Speed of Life!

ቦርዱ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ጋር ምክክር እያካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 19፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ጋር ምክክር እያደረገ ነው።

ቦርዱ አካል ጉዳተኞች በምርጫ ሂደት ስላላቸው ተሳትፎ እንዲሁም በአዲሱ የምርጫ ህግ አካታችነት ዙሪያ ነው ውይይቱን እያደረገ ያለው።

በምክክር መድረኩ ላይ ከቦርዱ አመራሮችና ሰራተኞች፣ ከክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተወጣጡ ሰራተኞች፣ ከኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ ማህበራት ፌዴሬሽን እንዲሁም ከተለያዩ የአካል ጉዳተኛ ማህበራት ተወካዮች እየተሳተፉ ነው።

በምክክሩ ላይ የቅድመ ምርጫ ዝግጅት ወቅት የተለያዩ ጥናቶች እና ስልጠናዎች ሲካሄዱ አካል ጉዳተኞችን የማካተት አስፈላጊነት ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል።

እንዲሁም አካታች የምርጫ ህግና ፖሊሲ ማዕቀፎች አስፈላጊነት እና የምርጫ ስፍራዎች አመችነት፣ በምርጫ ታዛቢነት መካፈል እንዲሁም የተለያዩ ሀገራት በምርጫ ሂደት እና ያላቸውን ተሞክሮ መዳሰስ እንደሚገኝበት ከቦርዱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!
https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.