Fana: At a Speed of Life!

በመሬት መንሸራተት ጉዳት ደርሶበት የነበረው የሱልልታ -ደብረ ማርቆስ ኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 27 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በመሬት መንሸራተት የተነሳ ጉዳት ደርሶበት የነበረው የሱልልታ -ደብረ ማርቆስ ባለ 400 ኪሎ ቮልት የከፍተኛ ኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ መስመር ጥገና ተጠናቀቀ ።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንደገለጸው፥ ለጥገና ሥራው ሲባል ብሔራዊ የኃይል ማዕቀፉ (ግሪድ) ለሁለት ተከፍሎ ከመጋቢት 20 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ጥገናው ሲከናወን ቆይቷል።

በዚህም በማዕቀፉ ላይ የደረሰው ጫና ከ4 በመቶ ሳይበልጥና የጎላ የኃይል መቆራረጥ ሳያጋጥም ዛሬ የጥገና ሥራው ሙሉ በሙሉ ተጠናቅቋል።

ጥገናው በተቋሙ የራስ ኃይል የኮንስትራክሽን ቢሮ ስምንት ሚሊየን ብር በጀት ተይዞለት የተሰራ ሲሆን በውጭ ሀገር ተቋራጭ ቢሰራ ከአንድ ሚሊየን ዶላር ወይም ወደ ሃምሳ ሚሊየን ብር ይጠይቅ እንደነበር ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.