Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድርን ታስተናግዳለች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በሴካፋ ስር ከሚደረጉ ውድድሮች አንዱ የሆነውን ከ17 አመት በታች የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድርን ታስተናግዳለች፡፡

በምስራቅና መካከለኛው አፍሪካ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖች የተዋቀረው ሴካፋ በስሩ የሚደረጉ 7 ወድድሮችን የሚያስተናግዱ ሀገራት ዝርዝር ይፋ አድርጓል።

የሴካፋ ዋና ዳይሬክተር አውካ ጌቼዮ እንደተናገሩት፥ ባለፉት ወራት ውድድር ለማዘጋጀት ጥያቄ ያቀረቡ ሀገራትን ለመምረጥ በትናንትናው እለት ስብሰባ ተደርጎ ሃገራቱ ተለይተው ተመርጠዋል።

በውሳኔው መሰረትም ኢትዮጵያ ከ17 አመት በታች የሚደረገውን የምስራቅ እና መካከለኛው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድር እንደምታስተናግድ ተገልጿል፡፡

ዩጋንዳ የሴቶችን የሴካፋ ውድድር እና የምስራቅና መካከለኛው አፍሪካን ፓን አፍሪካኒዝም ማጣሪያ ውድድርን የምታስተናግድ ሲሆን ሱዳን ደግሞ ከ20 አመት በታች የሴካፋ ዋንጫ ማጣሪያ ውድድርን የምታስተናግድ ይሆናል፡፡

ታንዛኒያ ደግሞ የሴቶች ቻምፒዮንስ ሊግ፣ ከ23 አመት በታች የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያን እና ካጋሜ ዋንጫን እንደምታስተናግድ ተመላክቷል፡፡

በወጣው መርሃ ግብር መሰረት የውድድር ቀናቶች በቀጣይ ይፋ እንደሚደረጉ ከሴካፋ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.