Fana: At a Speed of Life!

ወጋየሁ በኃይሉ – የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የማስተር የአሠልጣኝነት ደረጃ ያገኘ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 28 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ወጋየሁ በኃይሉ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የማስተር የአሰልጣኝነት ደረጃን ያገኙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ  ሆነዋል።

የኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር ማዕረግ የነበራቸው ወጋየሁ በኃይሉ ÷ ትናንት የነበራቸውን የተግባር ፈተና በብቃት በመወጣት ወደ ማስተር (ደረጃ ሰባት) ከፍ ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

አሰልጣኙን በተግባር ፈተና የመዘኑት ግራንድ ማስተር ፖል ዋይለር ግራንድ ማስተር ኡንግ ኪም ላንና ግራንድ ማስተር ሄክቶር ሞራኖ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በዚሁ መሰረት ወጋየሁ በኃይሉ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የማስተር ማዕረግ ያገኙ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንና በአፍሪካም እስከ አሁን የማስተር ነት ደረጃን ያገኘ አሰልጣኝ አለመኖሩን ኢዜአ አመልክቷል፡፡

በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የማስተር ማዕረግ ከዚህ በፊት ያገኘ ኢትዮጵያዊና አፍሪካዊ አሠልጣኝ እንደሌለ የዓለም አቀፉ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ድረ ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.