Fana: At a Speed of Life!

“ባክዶር” ምንድን ነው?

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 29፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) “ባክዶር” ማለት ወደ አንድ የኮምፒውተር ስርዓት ማለትም ኦፕሬቲንግ ሲስተም፣ አፕሊኬሽን ወይም ኔትዎርክ ለመግባት የደህንነት ወይም መደበኛ የደህንነት ማረጋገጫ ዘዴዎችን ለማለፍ የሚያስችል ምስጢራዊ የሆነ የመግቢያ መንገድ ነው።

ይህም ራሱን የቻለ ፕሮግራም ወይም የሌላ ፕሮግራም አካል ሆኖ የሚፈለገውን ስራ መስራት ያስችላል።

ለዚህም መረጃ መንታፊዎች ተጋላጭ የሆኑ የኔትዎርክ ክፍሎችን ወይም የዌብ አፕልኬሽኖችን ለመቆጣጠር ማልዌርን በመጠቀም ባክ ዶርን ይጭናሉ፡፡  ይህም የታለሙ ጥቃቶችን እንዲፈጽሙ ያስችላቸዋል።

ከኢንፎርሜሽን መረብ ደኅንነት አስተዳደር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው ዋና ዋናዎቹ ለባክ ዶር ጥቃት ከሚያጋልጡ መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡፡

  • ክፍት የሆኑ ፖርቶች
  • ደካማ የይለፍ ቃላት
  • ጊዜ ያለፈባቸው ሶፍትዌሮች፣ ተሰኪዎች
  • ደካማ ፋየርዎሎች
  • ትክክለኛ ያልሆነ መተግበርያዎች መጫን
  • የመግብያ ቦታዎች
  • እንዲሁም በኔትዎርክዎ ወይም ፕሮግራምዎ የደህንነት ክፍተት ወይም ተጋላጭነት ሲኖር መረጃ መንታፊዎች በባክ ዶሮች አማካኝነት አጥፊ ሶፍትዌር ፕሮግራሞችን በመጫን ወደ ፋይል ሰርቨሮችና ዳታቤዞች በመግባት ኮዶችን በመቀየር፣ የስርዓት ቅንብሮችን ለውጥ በማድረግ ሚስጥራዊ መረጃዎችን በርቀት ለመውሰድ የሚያስችሏቸው የተለያዩ ትዕዛዞች ተግባራዊ ለማድረግ ይጠቀሙበታል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.