Fana: At a Speed of Life!

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእግር ኳስ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፍ ይደረጋል – የእግር ኳስ ፌዴሬሽን

 

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 30፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በእግር ኳስ ስፖርት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

በፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የተመራ ልዑክ በአሶሳ ከተማ ከ15 ዓመት በታች ለሚገኙ ፓይለት ፕሮጀክት የኳስ እና ኮን ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ ርክክቡ ወቅት አቶ ኢሳያስ ጅራ አንደገለጹት÷ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ለክለቦች እና ብሄራዊ ቡድን በምርጥ ብቃት የሚጫወቱ ልጆችን ያፈራ መሆኑን አስታውሰው፤ ተተኪዎችን ለማፍራት በተያዘው ዕቅድ ከክልሉ ብቃት ያላቸው ልጆችን ለማግኘት ፌዴሬሽኑ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል፡፡

በወቅቱ የተጎበኙት የፓይለት ፕሮጀክት ሰልጣኞች እና አሰልጣኞች÷ ድጋፉ በስልጠና ወቅት ችግር የነበረውን የኳስ እጥረት በመቅረፍ ተገቢውን ስልጠና ለማካሄድ እደሚያግዝ መናገራቸውን የክልሉ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

የስልጠና ሜዳ እጥረትን ለመቅረፍ በአሕመድ ናስር መታሰቢያ ስታዲየም ጀርባ የሚገኘውን የድሮው የገበያ ቦታ በማስተካከል ለእግርኳስ ስልጠና እንዲውል ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አብዱልሙኒየም አደም ገልፀዋል።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.