Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን አቶ ታምራት ፈይሳን በድጋሜ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

 

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 1፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አቶ ታምራት ፈይሳ የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ለሁለተኛ ጊዜ ተመርጠዋል።

ጠቅላላ ጉባኤው ባካሄደው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫ÷ አቶ ታምራት ፈይሳ የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽንን ለቀጣይ አራት ዓመታት እንዲመሩ መርጧቸዋል። አቶ ታምራት ላለፉት አራት ዓመታት  ፌዴሬሽኑን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸውን አስታውሶ ዘገበው ኢዜአ ነው።

በጉባኤው ላይ ባለፈው ዓመት በፌደሬሽኑ አባል አገራት የነበረው የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት እንቅስቃሴና የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በስፖርቱ ላይ ያደረሰውን ተጽእኖ አስመልክቶ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በአምስተኛው የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ግራንድ ማስተር ፖል ዋይለርና ሌሎች የፌዴሬሽኑ አመራሮች ተገኝተዋል።

የአፍሪካ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን እ.አ.አ በ2016 የተቋቋመ ሲሆን ኢትዮጵያ፣ ብሩንዳ፣ ኮትዲቭዋር፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ጅቡቲ፣ ጋምቢያ፣ ሞዛምቢክ፣ ሴኔጋል፣ ሶማሌላንድ፣ ኡጋንዳና ታንዛንያ የፌዴሬሽኑ አባል ናቸው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.