Fana: At a Speed of Life!

በ2022ቱ የሆላንድ ሮተርዳም ማራቶን አትሌት ፌቨን ሃይሉ አሸነፈች

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 2፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ በሆላንድ በሚከናወነው የሮተርዳም ማራቶን በሴቶች ምድብ ኢትዮጵዊቷ አትሌት ፌቨን ሃይሉ አሸንፋለች፡፡
 
ፌቨን ርቀቱን በ2 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ከ01 ማይክሮ ሰከንድ በማጠናቀቅ ነው አሸናፊ የሆነችው፡፡
 
በወንዶች ምድብ በተከናወነው የማራቶን ውድድር ደግሞ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለሆላንድ የሚሮጠው አብዲ ነገያ አሸንፏል፡፡
 
ልኡል ገብረስላሴ ከኢትዮጵያ ሁለተኛ፣ ኪፕየጎ ከኬንያ ሦስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከሮተርዳም ማራቶን 2022 ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
በተመሳሳይ በስፔን ማርካሎ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ውድድር በሴቶች ምድብ አሚናት አህመድ ርቀቱን በአንደኝነት አጠናቅቃለች፡፡
 
በወንዶች ምድብ ደመቀ ታደሰ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ÷ ተስፋሁን አካልነው ደግሞ ሦስተኛ ሆኖ ጨርሷል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.