Fana: At a Speed of Life!

በፕሪሚየር ሊጉ ፋሲል ከነማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛ ሳምንት የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ፋሲል ከነማ ወደ አሸነፊነት የተመለሰበትን ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ፋሲል ከነማን ከጅማ አባ ጅፋር ያገናኘው ጨዋታ በፋሲል ከነማ 2 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

ጅማ አባ ጅፋር ሙሃመድ ኑር ናስር ባስቆጠራት ጎል እስከ እረፍት ሲመራ ቢቆይም ከእረፍት መልስ ይሁን እንዳሻው እና ኦኪኪ ኦፎላቢ ባስቆጠሯቸው ጎሎች ፋሲል 3 ነጥብ ማግኘት ችሏል፡፡

ማምሻውን በተካሄደ ጨዋታ ደግሞ ሲዳማ ቡና ሐዋሳ ከተማን አሸንፏል።

ሲዳማ ጨዋታውን 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ሙሉዓለም መስፍን፣ ዳዊት ተፈራ እና ይገዙ ቦጋለ የድል ጎሎቹን አስቆጥረዋል።

መስፍን ታፈሰ ደግሞ ለሐዋሳ ከተማ የማስተዛዘኛዋን ጎል አስቆጥሯል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.