Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ለተጎዱ ወገኖች ከ44 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ድጋፍ አደረገ፡፡

በኮሚሽኑ የሰሜን ወሎ፣ የደቡብ ወሎ ዞን የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር የልማት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ካሳ ተስፋ÷ ኮሚሽኑ ድጋፍ ያደረገው በጉባላፍቶ፣ ሀብሩና ራያ ቆቦ ወረዳዎች በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ነው ብለዋል።

በአሸባሪው የህወሓት ቡድን የተጎዱ የመሠረተ ልማት ተቋማትን በመገንባት ኮሚሽኑ ኃላፊነቱን ይወጣልም ነው ያሉት።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አቶ ይልቃል ሽፈራው በበኩላቸው÷ ባለፉት 50 ዓመታት ኮሚሽኑ በሰው ሠራሽና በተፈጥሮ አደጋ በሚከሰቱ ችግሮች የተጎዱ ወገኖችን በዘላቂነት ሲያቋቁምና የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ሲያከናውን መቆየቱን ተናግረዋል።

አሁንም ለችግር የተጋለጡ የህብረተሰብ ክፍሎችን በመደገፍ በዘላቂነት እንዲቋቋሙ ኮሚሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንደሚወጣ መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ድጋፍ የተደረላቸው ወገኖች የቤተክርስቲያኗ የልማት ድርጅት ኃይማኖት ሳይለይ ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.