Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ኢትዮጵያ እና እስራኤል የበለጠ ተቀራርበው ሊሠሩ ይገባል አሉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 6፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያ እና እስራኤል በጤና፣ በግብርና እና በኢንቨስትመንት ዘርፎች የበለጠ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸው ተናገሩ፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በአቶ ጋዲ ይባርከን የእስራኤል ፓርላማ አባልና የእስራኤልና ኢትዮጵያ የወዳጅነት ኮሚቴ ሰብሳቢ የሚመራና የፖርላማ አባላት እንዲሁም ከተለያዩ የሕክምና ተቋማት የተውጣጡ የልዑካን ቡድን አባላትን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በሰሜን ኢትዮጵያ በተካሄደው ግጭት የአስቸኳይ ዕርዳታ ለማስገኘት፣ የወደሙ የጤናና የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት፣ ሥልጠና ለመስጠት፣ ዘላቂ ድጋፍ ለማድረግ ያስችላቸው ዘንድ የመስክ ጉብኝት ማድረጋቸውን አብራርተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ የኢትዮጵያና የእስራኤል ግንኙነት ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ መሆኑን ገልጸው÷ እንዲህ ዓይነት የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት የበለጠ ጠንካራ መሠረት ላይ እንደሚስቀምጠውም አብራርተዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ ኢትዮጵያን በመጎብኘቱ አመስግነው÷ እንደዚህ ያለ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ውጤት ሊያስገኝ እንደሚችል ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ከፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ሁለቱ አገሮች በጤና፣ በግብርና እና በኢንቨስትመንት የበለጠ ተቀራርበው መሥራት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.