Fana: At a Speed of Life!

የጥቁር ህዝቦች የታሪክ ፣ የቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከልን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዙ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ለጥቁር ህዝቦች ታሪክ፣ ቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል ምሥረታ ሂደት መፋጠን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡

አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ ከጥቁር ህዝቦች የህግ፣ የታሪክና የማኅበራዊ ሣይንስ ምሁራን ጋር ለንደን በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወያይተዋል፡፡

በውይታቸውም ምሁራኑ የጥቁር ህዝቦችን የታሪክ ፣ የቅርስ ማቆያና የትምህርት ማዕከል በአዲስ አበባ ለማቋቋም የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚደግፉ ተናግረዋል።

የምሁራኑ ዓላማ ጥቁር ህዝቦች ላይ የተጫነውን የበታችነት ስሜት ለመቅረፍ የሚያስችል በመሆኑ አዲስ አበባ ላይ ማዕከሉን ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት እንደሚደግፉ አረጋግጠዋል፡

የጥቁር ህዝቦች ታሪክ ምሁር የሆኑት ደራሲ ሮቢን ዎከር ÷ ከድህረ ቅኝ ግዛት በኋላ በጥቁር ህዝቦች ላይ ያተኮረው ትርክት እጅግ የተዛባና በረቀቀ መልክ የበታችነት ስሜትን ለማስረጽ ያቀደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ጥቁር ምሁራን በሚያደርጉት ያላሰለሰ ጥረት ጥቁር ህዝቦች በራስ መተማመን ላይ የተመሰረተ ሥነ – ልቦና መላበስ ወቅቱ የሚጠይቀው ጉዳይ መሆኑንም አንስተዋል።

ለዚህም ከቅኝ ግዛት በፊት የነበረውን የጥቁር ህዝቦች ታሪክና ቅርስ መመርመር የሚያስችል ማዕከል አዲስ አበባ ላይ መመስረት ወሳኝ መሆኑን አመላክተዋል።

ለንደን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲም ቡድኑ ማዕከሉን በአዲስ አበባ ለማቋቋም የሚያደርገውን ጥረት እንደሚደግፍ አስታውቋል፡፡

የቡድኑ አስተባባሪ ትውልደ ኢትዮጵያዊው ጸጋዬ ጫማ በበኩላቸው ቡድኑ አባላቱን በመያዝ የማዕከሉን ምሥረታ ለማቀላጠፍ ወደ አዲስ አበባ እንደሚጓዝ ገልጸው ለተደረገላቸው ትብብር ማመስገናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.