Fana: At a Speed of Life!

1 ሺህ 250 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በሦስት ዙር በተከናወነ በረራ ዜጎችን ከሳዑዲ ዓረቢያ የመመለስ ስራ 1 ሺህ 250 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
ከእነዚህ ውስጥ 674 ሴቶች፣ 366 ሕጻናትና ቀሪዎቹ ወንዶች መሆናቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
መንግሥት በሳዑዲ አረቢያ በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሚመራና 16 መንግስታዊ መስሪያ ቤቶችን በአባልነት ያቀፈ ብሔራዊ ኮሚቴ በማዋቀር 102 ሺህ ዜጎችን ወደ ሃገር ለመመለስ በማቀድ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል ።
እስካሁን ድረስ በተከናወነ ዜጎችን የመመለስ ስራም ከ 9 ሺህ 700 በላይ ኢትዮጵያውያንን መመለስ ተችሏል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.