Fana: At a Speed of Life!

የጉምሩክ ኮሚሽን በ9 ወራት ውስጥ 103 ቢሊየን ብር ገቢ ሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉምሩክ ኮሚሽን በዘንድሮው በጀት ዓመት 9 ወራት ውስጥ 103 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡና አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሰሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር 23 በመቶ የሚጠጋ ብልጫ እንዳለው ተገለጸ።

የጉምሩክ ኮሚሽን የ2014 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈፃፀሙን እየገመገመ ይገኛል፡፡

ኮሚሽኑ በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጸጸሙ ከ103 ቢሊየን ብር ሲሰበስብ ፥ አፈጻጸሙም በመቶኛ ሲሰላ 87.3 በመቶ ሲሆን ፥ ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ22.8 በመቶ ብልጫ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡

በእቅድ አፈፃፀም ውይይቱ ላይ በኮሚሽኑ የሕግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ሙሉጌታ በየነ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፥ የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል፣ አሰራርን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማስደገፍና የቁጥጥር ስራዎችን ከማዘመንና አገልግሎቱን ለማፋጠን በዘጠኝ ወራቱ በትኩረት መሰራቱን አንስተዋል፡፡

ከገቢና ወጪ ኮንትሮባንድ 3 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር የሚጠጉ የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዛቸውም በሪፖርቱ ተመላክቷል፡፡

የዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጸጸም ሪፖርቱን ያቀረቡት በኮሚሽኑ የስትራቴጂክ ፕላንና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ አብዲሳ ዱፌራ ፥ በዘጠኝ ወራት ውስጥ 1 ነጥብ 8 ሚሊየን አገልግሎቶችን መስጠት መቻሉን እና የአቤቱታ ምላሽ አሰጣጥን በማሳደግ 97 በመቶ ማድረስ ተችሏል ብለዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ፥ የገቢ አፈፃፀሙ አሁን ላይ ኢትዮጵያ ካጋጠማት የፀጥታ ችግርና የተወሰኑ የገቢ ሰብሳቢ ተቋማት ስራ ባቆሙበት ወቅት የተመዘገበ ውጤት በመሆኑ አፈፃፀሙ አበረታች እንደሆነ መግለጻቸውን ከገቢዎች ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.