Fana: At a Speed of Life!

መገናኛ ብዙኃን ለሠላም ጋዜጠኝነት ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መገናኛ ብዙሃን የሰላም ጋዜጠኝነት ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ በኦሮሚያ በተካሄደ የውይይት መድረክ ላይ ተገለጸ።

የ”ጉሚ በለል” ውይይት “የሰላም መሰረተ ልማት ግንባታ እና የሚዲያ ሚና” በሚል መሪ ሀሳብ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዛሬ ተካሂዷል።

የውይይቱ ተሳታፊዎችም መገናኛ ብዙኃን የግጭትና የጦርነት ዘገባ ላይ ማተኮሩን ትተው ለሀገራችን የሰላም ግንባታ አስተዋጽኦ ላለው “በሰላም ጋዜጠኝነት” ላይ ትኩረት ሰጥተው መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ የመነሻ ጽሁፍ ያቀረቡት የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር ዶክተር ሮባ ጴጥሮስ ÷ “የምድራችን ጦርነቶች ሁሉ መነሻ የሰው ልጅ አእምሮ ነው፤ የሰላምም መነሻው ይኸው አእምሮ ነው” ብለዋል፡፡

በመሆኑም መገናኛ ብዙኃኑ የሰላም ጋዜጠኝነት ላይ በመሥራት ዜጎች በሀገሪቷ ለተፈጠሩ ችግሮች ከጠመንጃ ይልቅ በውይይት መፍታት እንደሚቻል ግንዛቤ ሊፈጥሩ እንደሚገባ ነው ያሳሰቡት፡፡

በተጨማሪም መገናኛ ብዙኃኑ በሰላም ጋዜጠኝነት ÷ መንግስትንና ህዝብን ማቀራረብ እና በትብብር እንዲሰሩ ማድረግ እንደሚገባም ምሁሩ ጠቁመዋል፡፡

በጽሑፍ ያሉ የተሳሳቱ ተረኮችና ታሪኮችንም በማረም ረገድ መገናኛ ብዙኃኑ ከፍተኛ ሚና መወጣት እንደሚገባቸውም የህግ ምሁሩ ማሳሰባቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

የኦቢኤን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ አስራት ÷ በበኩላቸው ምንም እንኳን የግል መገናኛ ብዙኃን በቁጥር እየተበራከቱ ቢመጡም የአገሪቱን ህግና የሙያውን ስነ ምግባር እንዲሁም የኤዲቶርያል ፖሊሲውን አክብሮ ከመንቀሳቀስ አኳያ ክፍተት የሚታይባቸው በመሆኑ ማስያዝና ማስተካከል እንደሚገባ ጠቁመዋል።

መገናኛ ብዙሃን በተለይ በብሔራዊ ምክክሩ ሀገራዊ መግባባትን የመፍጠር ግብ ለማሳካት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም አሳስበዋል።

“ጉሚ በለል” በክልሉ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የሚዘጋጅና በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳዮች የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላትና ምሁራን ሃሳብ አስተያየታቸውን በነፃነት የሚገልጹበት ወርሃዊ መድረክ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.