የ2022 ካዛኪስታን – ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀናቸው
አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የ2022 ካዛኪስታን – ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል ቀንቷቸዋል፡፡
በሴቶች አትሌት በቀሉ አበበ የ2022 ካዛኪስታን – ዱሻንቤ ኢንተርናሽናል ግማሽ ማራቶን ውድድር አሸናፊ ሆናለች፡፡
በተመሳሳይ መርሐ ግብር በወንዶች አትሌት ግርማ ጥላሁን ሁለተኛ ደረጃን በማግኘት ውድድሩን ማጠናቀቁን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በሌላ በኩል በዓለም አትሌቲክስ የፕላቲኒየም ደረጃ በተሰጠው የ2022 የደቡብ ኮርያ – ሴኡል ማራቶን በወንዶች አትሌት ሞስነት ገረመው የቦታውን ሰዓት በማሻሻል እና 2 ሰዓት 4 ደቂቃ 43 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት አሸንፏል፡፡
በተመሳሳይ በዚሁ የውድድር መርሐ ግብር ሄርጳሳ ነጋሳ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!