Fana: At a Speed of Life!

በሐዋሳ ከተማ ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የመላ ኢትዮጵያ ሴቶች ጨዋታ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ከሚያዝያ 1 እስከ 9 ቀን 2014 ዓ.ም “የሴቶች እኩል ተሳታፊነት ለስፖርት ውጤታማነት” በሚል መሪ ቃል ለአንድ ሳምንት ሲካሄድ የቆየው 4ኛው የመላ ሴቶች ጨዋታ ተጠናቋል።
ኦሮሚያን ከሲዳማ ባገናኘው የፍጻሜ የእግር ኳስ ጨዋታ ኦሮሚያ 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸናፊ ሆኗል፡፡ በዚህም ኦሮሚያ የወርቅ፣ ሲዳማ የብር፣ አዲስ አበባ የነሐስ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በባህል ስፖርቶች ውድድር ኦሮሚያ 1ኛ፣ ሲዳማ 2ኛ እና አዲስ አበባ 3ኛ ሆነዋል።
በፖራሊምፒክ ስፖርቶች ኦሮሚያ፣ ደቡብ እና ሲዳማ በቅደም ተከተላቸው ከ1 እስከ 3 ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድራቸውን ሲያጠናቅቁ÷ መስማት በተሳናቸው ስፖርቶች ኦሮሚያ 1ኛ ሲሆን ሲዳማ እና አዲስ አበባ 2ኛና 3ኛ ሆነዋል።
በአጠቃላይ የኦሊምፒክ ስፖርቶች ኦሮሚያ አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን÷ አዲስ አበባ 2ኛ ደቡብ ክልል 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።
አሸናፊ ክልሎች የተዘጋጀላቸውን ሜዳሊያና ዋንጫ ከዕለቱ የክብር እንግዳ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት እና ሌሎች እንግዶች እጅ ተረክበዋል።
በ10 የስፖርት ዓይነቶች በተካሄደው 4ኛው መላ ኢትዮጵያ የሴቶች ጨዋታ ከደቡብ፣ ከሐረሪ፣ ከአዲስ አበባ፣ ከድሬዳዋ፣ ከኦሮሚያ፣ ከሲዳማ፣ ከጋምቤላ እና ከሱማሌ የተውጣጡ ከ1 ሺህ በላይ ስፖርተኞችና ልዑካን ቡድን አባላት መሳተፋቸውን ከባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.