Fana: At a Speed of Life!

የአሉቶ ላንጋኖ የከርሰ ምድር እንፋሎት የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንደኛው ጉድጓድ የምርት ሙከራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሉቶ ላንጋኖ የከርሰ ምድር እንፋሎት የማስፋፊያ ፕሮጀክት በአንደኛው ጉድጓድ የምርት ሙከራ በይፋ ጀመረ፡፡

የአሉቶ የከርሰምድር እንፋሎት ፍለጋ ቁፋሮ ከተጠናቀቀባቸው አራት ጉድጓዶች መካከል አንደኛው የምርት ሙከራ በይፋ መጀመሩን የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ መሳይ ፍቃዱ አስታውቀዋል፡፡

ሥራ አስኪያጁ እንደገለፁት ፥ የአምስተኛው ጉድጓድ ቁፋሮ 700 ሜትር ላይ ደርሷል፡፡

ግንቦት 21 ቀን 2013 ዓ.ም በይፋ የተጀመረው የአሉቶ ላንጋኖ የከርሰ ምድር እንፋሎት የማስፋፊያ ፕሮጀክት ስድስተኛውን የእንፋሎት ፍለጋ ጉድጓድ ቁፋሮ ለማስጀመር የመቆፈሪያ ማሽን (ሪግ) ወደሚቆፈረው ቦታ በማንቀሳቀስ የመትከል ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አንድ ጉድጓድ ለመቆፈር በአማካይ እስከ 75 ቀናት ይፈጃል ያሉት አቶ መሳይ ፥ ቁፋሯቸው ከተጠናቀቁት አራት ጉድጓዶች መካከል የሁለተኛው ጉድጓድ የምርት ሙከራ ሥራ ከሁለት ሳምንት በኋላ ይጀመራል ብለዋል፡፡

የእንፋሎት ፍለጋ የጉድጓድ ቁፋሮው ወደ ከርሰ ምድር እስከ 3 ሺህ ሜትር ጥልቀት የሚኖረው ሲሆን ፥ ፕሮጀክቱ እስከ 70 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ ሃይል ለማመንጨት ታስቦ እየተሰራ መሆኑን ከኤሌክትሪክ ሃይል ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.