Fana: At a Speed of Life!

የማዳበሪያ ፍላጎትን በዘላቂነት ለመፍታት እና የአፈርን ለምነት ለመጠበቅ በትኩረት መሰራት አለበት- ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የማዳበሪያ ፍላጎትን በዘላቂነት ለመፍታት እና የአፈርንም ለምነት ለመጠበቅ በትኩረት መሰራት እንዳለበት የግብርና ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ሚኒስቴሩ የአፈር ለምነትን ለመጠበቅና የሚፈለገውን ምርት ለማምረት በሚያስችል ጉዳይ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተወያየ ነው፡፡
በውይይቱም÷ በተለይም አሁን ላይ እያጋጠመ ካለው የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ አቅርቦት ጋር በተያያዘ ያለውን ችግር በመፍታት እና የአፈርን ለምነት በተፈጥሮአዊ መንገድ ለመጠበቅ በትኩረት መሰራት እንደሚገባ ተመላክቷል።
በተለይም የተፈጥሮ ማዳበሪያን (ኮምፖስትን) የማዘጋጀት ልምድንም ከፍ ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት መሆኑ ተገልጿል፡፡
በውይይቱ ላይ የተፈጥሮ ሃብት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር ኢያሱ ኤልያስ ባደረጉት ንግግር÷ ኢትዮጵያ የምግብ ፍጆታዋን በራሷ ለመሸፈን የበጋ መስኖን በማሳደግ የመኸር ሰብልን ለማሳደግ ትልቅ ትኩረት ሰጥታ እየሠራች መሆኗ ገልጸው፥ በዚህ ስራም ማዳበሪያ ትልቁ ግብአት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
ስለሆነም ከዚህ በፊት የነበሩ የተፈጥሮ ማዳበሪያን የማዘጋጀት ልምድን የበለጠ በማሳደግ ከሚቀርበው የሰው ሰራሽ ማዳበሪያ ጋር አጣምሮ የማዳበሪያ ተጠቃሚነት ፍላጎትን ለማሳካት በትኩረት መስራት ያስፈልጋል ነው ያሉት፡፡
አክለውም የማዳበሪያ ፍላጎትን በዘላቂነት ለመፍታት እና የአፈርንም ለምነት ለመጠበቅ መሰራት ያለበት ጉዳይ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
በይስማው አደራው
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.