Fana: At a Speed of Life!

ለላሊበላ ከተማ ከ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጡ የውሃ ፓምፖች ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የላሊበላ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ሲ አር ኤስ ከተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተገዙ የንጹህ መጠጥ ውሃን ለማህበረሰቡ ማድረስ የሚያግዙ ማሽኖች ድጋፍ ተደርጎለታል፡፡
 
የጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ መለሰ አየለ÷ በአሸባሪው እና ወራሪው ህወሓት ጉዳት ከደረሰባቸው ተቋማት አንዱ የሆነው የላሊበላ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ጽህፈት ቤት ከተሽከርካሪ ጀምሮ በርካታ ትላልቅ ንብረቶች የተዘረፉበት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡
 
በተቋሙ የነበሩት ንብረቶች ሙሉ በሙሉ በዘራፊው ሃይል መወሰዳቸውን ጠቁመው÷ በገንዘብ ሲገመት ከ26 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆን ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።
 
ተቋሙ ውስጥ ምንም አይነት እቃ ያልተረፈ በመሆኑ የንፁህ መጠጥ ውሀን ለማህበረሰቡ ለማድረስ አስቸጋሪ አድርጎት ነበር ያሉት ስራ አስኪያጁ÷ መብራት ባለመኖሩ ከክልሉ ውሃ ቢሮና ሌሎች መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር የመጠጥ ውሃን ለማህበረሰቡ ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
 
አሁን ላይም ተቋሙ ሲ አር ኤስ ከተባለ ድርጅት ዋጋቸው ከ11 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ ተጨማሪ ጀኔነተር ፣ ሰርፌስ ፓምፕ፣ ጠላቂ ፓምፕ እና ሌሎችንም እቃዎች ድጋፍ እንደተረገለት ተናግረዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍም ተቋሙ የነበረበትን ችግር በተወሰነ ደረጃ የሚቀርፍ እንደሆነ መግለጻቸውን ከላሊበላ ከተማ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.