Fana: At a Speed of Life!

በ2014 የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ያደረጉ የግል ትምህርት ቤቶች በቀጣዩ የትምህርት ዘመን ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ ተገለፀ፡፡

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የ2015 የትምህርት ዘመንን የክፍያ ጭማሪ አስመልክቶ ከትምህርት ቤቶቹ ጋር ባደረገው ምክክር፥ በ2014 ዓ.ም ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች በ2015 የትምህርት ዘመን ምንም ዓይንት ጭማሪ ማድረግ እንደማይችሉ የባለስልጣኑ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ህይወት ጉግሳ ተናገረዋል፡፡

ነገር ግን ላለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ጭማሪ ሳያደርጉ የቆዩ ትምህርት ቤቶች በሚያቀርቡት ፕሮፖዛል እና ከወላጅ ጋር በሚያደርጉት መግባባት መሰረት ጭማሪ ማድረግ እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡

የአዲስ አበባ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ፍቅርተ አበራ÷ከመደበኛ የአገልግሎት ክፍያ ውጭ በአይነትም ሆነ በገንዘብ ትምህርት ቤቶች ክፍያ መጠየቅ አይችሉም ያሉ ሲሆን ÷ ከዚህ ቀደም ያለ አግባብ ጭማሪ ያደረጉ ትምህርት ቤቶች እርምት እንዲወስዱ መደረጉንም ገልጸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ቅርንጫፎቻቸውን ጨምሮ 2 ሺህ የሚጠጋ የግል ትምህርት ቤቶች ያሉ ሲሆን÷ እነዚህ ትምህርት ቤቶች 400 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ያስተናግዳሉ ፡፡

ይህም ከአጠቃላይ የአዲስ አበባ የተማሪ ሽፋን 43 በመቶውን የሚይዝ መሆኑን ከአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.