Fana: At a Speed of Life!

ኢሰመኮ ሁለተኛው የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ሆኖ ተመረጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሁለተኛው የአፍሪካ ብሔራዊ የሰብዓዊ መብቶች ተቋም ሆኖ ተመረጠ፡፡

በአፍሪካ ውስጥ እውቅና የተሰጠው ተቋም እንዲሆን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ለሕጻናት የሚያደርገው ጥበቃ እና የሚሰጠው የሰብዓዊ መብት ከለላ በአፍሪካ ሰብዓዊ መብት እና ደኅንነት ላይ በሚሰሩ የምሁራን ኮሚቴ መገምገሙን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአፍሪካ ደረጃ መመረጥ ከአህጉሩ የሕጻናት መብትና ደኅንነት ምሁራን ኮሚቴ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲያጠናክር ያስችለዋል ተብሏል።

ኮሚሽኑ ዕውቅናውን ያገኘው ከፈረንጆቹ መጋቢት 21 እስከ ሚያዝያ 1 ቀን 2022 ሲካሄድ በቆየው የኮሚቴው 39ኛ መደበኛ ጉባዔ ላይ ነው።

በአፍሪካ ሰብዓዊ መብት እና ደኅንነት ላይ የሚሰሩት ምሁራን ስብስብ በአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች እና ደህንነት ቻርተር መሰረት የሕጻናትን መብት እና ደኅንነት ለማስጠበቅ የተቋቋመ ኮሚቴ ነው፡፡

ቻርተሩ በአፍሪካ ኅብረት (በቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት) በፈረንጆቹ 1990 ተቀባይነት ካገኘ በኋላ ኢትዮጵያም በ2002 ተቀብላ በማጽደቅ እየተገበረችው ይገኛል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.