Fana: At a Speed of Life!

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ እና የቱርኩ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ጋር በጋራ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት ላይ ትኩረቱን ያደረገ የትብብር ስምምነት ተፈራርመዋል።

ስምምነቱን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር መሀመድ ኡስማን እና በኢትዮጵያ የቱርክ ማዐሪፍ ፋውንዴሽን ተወካይ ሌቬንት ሳሂን ተፈራርመዋል።

ሁለቱ ወገኖች በትምህርት፣ በምርምር፣ በባህልና በቋንቋ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት ነው የተስማሙት፡፡

በመግባቢያ ሰነዱ ላይ እንደተገለጸው ÷የሠመራ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ሰራተኞች በቱርክ የድህረ ምረቃ ትምህርቶችን የመከታተል እድሉ ይኖራቸዋል።

ማዐሪፍ ፋውንዴሽን የተቋቋመው በሰው ልጆች የጋራ እውቀት እና እሴቶች ላይ የተመሰረተ መደበኛ እና መደበኛ ያልሆኑ አገልግሎቶችን ለመስጠት መሆኑን ከዩኒቨርሲቲው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ግንኙነቱን ለማጠናከር በሚያደርገው ጥረት የዛሬውን ጨምሮ ቀደምሲል ከተለያዩ የቱርክ ተቋማት ጋር የትብብር ስምምነቶችን ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.