Fana: At a Speed of Life!

በሶማሌ ክልል ከ9 ቢሊየን ብር በላይ ካፒታል ላስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ሰጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ9 ቢሊየን ብር የሚበልጥ ካፒታል ላስመዘገቡ 381 ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ መስጠቱን የክልሉ ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታውቋል።
 
የቢሮው ምክትል ሃላፊ ወይዘሮ ዘይነባ ሀጂ አድን እንደገለጹት÷ የኢንቨስትመንት ፈቃዱ የተሰጠው ከሐምሌ 1 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ነው።
 
ባለሃብቶቹ በግብርና፣ ኢንዱስትሪ፣ ትራስፖርት፣ አገልግሎትና ሌሎችም የልማት ዘርፎች በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች ለመሰማራት የሚያስችል እቅድ አቅርበው እንደፀደቀላቸው ገልጸዋል።
 
በአሁኑ ወቅትም የፕሮጀክቶቻቸው ግንባታና ሂደት በተለያየ የአፈፃፀም ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የጠቀሱት ወይዘሮ ዘይነባ÷ በሙሉ አቅማቸው ወደ ስራ ሲገቡ ከ14 ሺህ ለሚበልጡ ሰዎች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።
 
የክልሉ መንግስት በከተሞች የመንገድ መሰረተ ልማት ማስፋፋቱ በተለይ ጅግጅጋ ከተማ የውስጥ ለውስጥ አስፓልት መንገድ መገንባቱ፣ ከምን ጊዜም በላይ ሰላምና መረጋጋት በክልሉ መኖሩ ለኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ምቹ ሁኔታ መፍጠሩን አስረድተዋል።
 
ባለሃብቶቹ በገቡት ውል መሰረት እቅዶቻቸውን ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ ነውም ብለዋል ምክትል ሃላፊዋ።
 
የክልሉ መንግስት ባለሃብቶች ራሳቸውን እና ማህበረሰቡን እንዲጠቅሙ የኢንቨስትመንት ስራዎች ፈቃድ ከመስጠት ጀምሮ የተለያዩ ማበረታቻዎች እንዲያገኙ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን መግለጹን ኢዜአ ዘግቧል።
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.