Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ክብረ ወሰን በማሻሻል አሸነፉ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት በተካሄዱ ዓለም አቀፍ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የቦታውን ክብረ ወሰን በማሻሻል ጭምር ውድድሮችን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡
በዚሁ መሰረት በሀምቡርግ ማራቶን÷ አትሌት ያለምዘርፍ የኋላው 2 ሰዓት ከ17 ደቂቃ ከ23 ሰከንድ በሆነ ጊዜ በመግባት እና የቦታውን የማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል አሸንፋለች፡፡
በተመሳሳይ በማድሪድ ማራቶን÷ አትሌት ሥራነሽ ይርጋ የቦታውን ሰዓት በማሻሻል ውድድሩን በበላይነት ስታጠናቅቅ÷ በዚሁ የውድድር መርሐ ግብር አትሌት መሰረት አበባየሁ ሁለተኛ ደረጃን ይዛለች፡፡
በኢንሼዴ ማራቶን÷ አትሌት አለምፀሐይ አሰፋ ሁለተኛ፣ አትሌት አበራሽ ፈይሳ አራተኛ ደረጃን ይዘው ውድድሩን ማጠናቀቃቸውን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በዚሁ መርሐ ግብር በወንዶች አትሌት ታዱ አባተ ሦስተኛ ደረጃን ይዟል፡፡
በቬና ማራቶን÷ በሴቶች አትሌት ኡርጌ ሰቦቃ አራተኛ ደረጃን ይዛ ውድድሩን አጠናቃለች፡፡
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.