Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የ8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሶማሌ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች የሚውል የ8 ሚሊየን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ድጋፉን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ደርቤ አስፋው ለሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፋ መሃመድ አስርክበዋል፡፡
 
አቶ ደርቤ የተደረገው ድጋፍ በክልሉ በተከሰተው ድርቅ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማቋቋም እየተደረገ ያለው ጥረት ለማገዝ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ርዕስ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ በበኩላቸው ÷ባንኩ በድርቅ ለተጎዱ ዜጎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን ከሶማሌ ብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.