Fana: At a Speed of Life!

ሰው አልባ አውሮፕላኖችን  ለሃገራዊ ልማትና ለሰብዓዊ አገልግሎት ለማዋል ሃገር አቀፍ የምክክር መድረክ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖች) ለሃገራዊ ልማት እና ለሰብዓዊ አገልግሎት ለማዋል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ሃገር አቀፍ ምክክር ተካሄደ።

 

መድረኩ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር እና በአለም የምግብ ፕሮግራም አስተባባሪነት የተዘጋጀ ሲሆን÷ሰው አልባ አውሮፕላኖች  በሃገራት የመከላከያ፣ የደህንነት፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ፣ የጂኦፖሊቲካዊ ጉዳዮች ላይ ሚናቸዉ እያደገ  መምጣቱን የአስተዳደሩ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ተናግረዋል።

 

የሰው አልባ አውሮፕላኖች ቴክኖሎጂ በስፋት ወታደራዊ  ተግባር ላይ በመዋል ቢታወቅም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን በሳይንስ፣ በንግድ፣ በግብርና፣ በጤና ጥበቃ፣ በመዝናኛ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛልም ብለዋል፡፡

 

የሰው አልባ አውሮፕላኖች  ወንጀለኛን ለመከታተል፣ የምርት አቅርቦት ዘርፍን ለማጎልበት፣ የሰላም ማስከበር እና የአየር ላይ ፎቶግራፍ ለማንሳት በስፋት እየዋሉ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

 

ከሰው አልባ አውሮፕላኖች የሚገኘዉን ጥቅም በአግባቡ ለማግኘት በሃገር አቀፍ ደረጃ የአጠቃቀም መመሪያ፣ ፖሊሲ እና ህግ እንደሚያስፈልግም ተመላክቷል።

 

 

መድረኩ ሰዉ አልባ አዉሮፕላኖችን ለልማት እና ለሰብዓዊ ተግባራት ለማዋል ጉዳዩ የሚመለከታቸዉን ባለድርሻ አካላት ያቀፈ ሃገራዊ ግብረ ሃይል ማቋቋምን ታሳቢ ያደረ መሆኑን ከአስተዳደሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ሃገር አቀፍ ግብረ-ሃይሉም  የማስተባበር፣ የድሮን አጠቃቀም ላይ ያተኮሩ ህጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ዝግጅት ላይ የመደገፍ እንዲሁም ህጎችን የማስፈጸም ስራ እንደሚሰሩ ተጠቅሷል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.