Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ትናንት ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 19 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ ትናንት ከተፈጠረው ችግር ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋልና ተጠያቂነት የማረጋገጥ ስራ መጀመሩን የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ጌታቸው ጀንበር ገለጹ።
 
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩና ሌሎች የክልሉ አመራሮች ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል፡፡
 
ውይይቱ ችግሩን ብስለት በተሞላበት ሁኔታ ለመፍታት፣አጥፊዎችን ተጠያቂ ለማድረግ እና የችግሩን መሰረት አውቆ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ያለመ ነው ተብሏል።
 
በውይይቱ መክፈቻ ላይ ዶክተር ጌታቸው ጀንበር ትናንት የተፈጠረው ችግር ሁሉንም የማይወክል አሳፋሪና አሳዛኝ ድርጊት ነው ብለዋል።
 
በችግሩ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር የማዋልና ተጠያቂነትን የማረጋገጥ ስራ መጀመሩንም ነው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ የተናገሩት፡፡
 
በምናለ አየነው
 
 
ኢትዮጵያን፦ እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
 
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.