Fana: At a Speed of Life!

የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም-ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 20፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለፁ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፥ እንደ ህዝብ ልዩነቶቻችንን አምነን ተቀብለን በብዙ ትውልዶች ዕድሜ በኁባሬ ተሣሥረን ኖረናል ብለዋል።

በጋራ ስፌታችን ውስጥ መቻቻል አንዱ አስፈላጊ ሰበዝ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ÷ እንደ አንድ ሕዝብ፣ የሀገራችንን መጥፋት የሚፈልጉ ሁሉ፣ የጥፋት ዕቅዳቸው ወኪል አድርገው እንዲወስዱን ልንፈቅድ አይገባም ነው ያሉት።

በአንዳንድ ማኅበረሰቦች ውስጥ እንዲሆን የምንፈቅድለት ክፋት ከእርስ በርስ ተዛምዷችን ጋር ካለው ቅርበት ይልቅ ለሌሎች የጥፋት ወኪሎች መጠቀሚያ የሚሆን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

በማኅበረሰባችን ውስጥ የአስተዋዮችን ልቡና እንፈልግ፤ ልዩነቶችን ከማጉላት ይልቅ ለማቀራረብ እንሥራ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል የምንጋራው ሰብአዊነት ይህንን እንድናደርግ ያስገድደናል በማለት።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማንንም ለማጥፋት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረግ ጥቃት በሁላችን ላይ የሚደረግ ነው ያሉ ሲሆን፥ አጥፊውን አውግዘን ከተጠቂው ጋር እንቆማለን እንጂ ጥፋቱን በሌላ ጥፋት ለማባባስ መሞከር የለብንም ብለዋል።

ከኢትዮጵያ ሰላም እንጂ ከኢትዮጵያ ሑከት ማናችንም አናተርፍም በማለትም አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.